ማስታወቂያ/Announcement

 

ጥቅምት 2ዐ ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም.

ማስታወቂያ

ቀደም ሲል በውጭ አገር ኖረው ወደ ሀገራቸው ጠቅልለው የሚመለሱ ኢትዮጵያውያንና ትውልድ ኢትዮጵያውያን መኪናን ጨምሮ የቤት ውስጥ መገልገያዎችን ከቀረጥ ነፃ እንዲያስገቡ የሚፈቅድ አሰራር ተግባራዊ ሲደረግ ቢቆይም አንዳንድ ተገልጋዮች የተሰጠውን እድል አለአግባብ በመጠቀማቸው ምክንያት እንዲቆም መደረጉ ይታወሳል፡፡

ይሁን እንጂ የቀረጥ ነጻ እድሉ እንዲቆም ሲደረግ ቀረጥ ከፍሎ ማስገባት የሚቻልበት አሰራር አብሮ የቆመ ባለመሆኑ በውጭ አገር አምስት ዓመትና ከዚያ በላይ ቆይተው ወደ ሀገር ጠቅልለው የሚመለሱ ኢትዮጵያውያን መኪናን ጨምሮ ሙሉ የቤት ውስጥ መገልገያ መሣሪያዎችን ቀረጥ ከፍለው ማስገባት የሚችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

ኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ኤምባሲ

ስቶክሆልም

 

۞►◄►◊◄►◄►◊◄►◊►◄►◊◄►◄►◊◄►◄►◊◄►◄►◊◄►◄►◄►◄►◊◄►۞

 

ማስታወቂያ

ነሐሴ 9 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም.

ጉዳዩ፡- በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልድ ኢትዮጵያውያን ምሁራን ወደ አገር ቤት መጥተው እንዲያገለግሉ ማድረግን ይመለከታል

 

የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከIOM ፣ ከUNDP እንዲሁም ከገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር የMigration for Development in Ethiopia በመቅረጽ በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልድ ኢትዮጵያውያን በእውቀት እና ቴክኖሎጂ ሽግግር የሰው ኃይል እጥረትን ለማቃለል እንዲቻል ፕሮጀክት ነድፎ በመንቀሳቀስ ላይ ነው፡፡ በዚሁ መሠረት ትኩረት በተሰጣቸው በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት፣ በጤና እንዲሁም በውሃ ስራ መስክ በውጭ አገር የሚገኙትና በከፍተኛ ደረጃ ሥልጠናና ልምድ ያካበቱ ኢትዮጵያውያንና ትውልድ ኢትዮጵያውያን ምሁራን ወደ አገር ቤት መጥተው እንዲያገለግሉ ለማድረግ ጥረት እየተደረገ ነው፡፡

ባለፈው ዓመት (በ2ዐዐ1 ዓ.ም.) በአሜሪካ የሚኖሩ ትውልድ ኢትዮጵያውያን የሕክምና ባለሙያዎችን በማምጣት አገልግሎት እንዲሰጡ የተደረገ ሲሆን በዚህ ዓመትም የፍላጐት ዳሰሳ በመካሄድ በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልድ ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገር ቤት መጥተው ማገልገል በሚፈልጉበት መስክ እንዲያገለግሉ ዝርዝር ተዘጋጅቷል፡፡

በዚህ ፕሮጀክት በኩል፡-

       ለተጠየቀው ሥራ ተሳትፎ ለሚያደርጉ እንዲሁም ለመስራት ከፈለጉበት ዩኒቨርስቲ ጋር ስምምነት ሲያደርጉ ካሉበት አገር ቤት ደርሶ መልስ የጉዞ ወጪ ይሸፍናሉ፡፡

       ዩኒቨርስቲዎች ለተመሳሳይ ሙያ ያላቸው የሚሰጡት የወር ደመወዝ ከሚያቀርቡላቸው የመኖሪያ ቤትና የአገር ውስጥ ትራንስፖርት በተጨማሪ Top up300USD/month ይሰጣሉ፡፡

       ቢያንስ ከ6 ወር በላይ ማገልገል ለሚፈልጉ ቅድሚያ ይሰጣል፡፡

በመሆኑም ፍላጐት ያላችሁ ባለሙያዎች በየትኛው ዩኒቨርስቲ/ተቋም በምን ዓይነት የትምህርት መስክ መሰማራት እንደምትፈልጉ እና መቼና ለምን ያህል ጊዜ በአገልግሎት እንደሚቆዩ የሚገልጽ ማመልከቻና CV ለኤምባሲያችን ወይም ለሚመለከተው ዩኒቨርስቲ ወይም ተቋም መላክ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

ለበለጠ መረጃ http://www.ethemb.se/ee_community.html

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ኤምባሲ

ስቶክሆልም

۞►◄►◊◄►◄►◊◄►◊►◄►◊◄►◄►◊◄►◄►◊◄►◊◄►◄►◊►►◊◄►◄►◊◄►۞

 

ማስታወቂያ

ነሐሴ 8 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም.

ጉዳዩ፡- በኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ወቅት ንብረታቸውን ትተው የወጡ ኤርትራውያንን ይመለከታል

 

ግንቦት 7 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም. የሚኒስትሮች ም/ቤት ባወጣው መመሪያ መሠረት በኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ወቅት ንብረታቸውን ሳይሸጡ ኢትዮጵያ ውስጥ ትተው የወጡ ኤርትራውያንን ንብረት መመለስ ስለሚቻልበት ሁኔታ መመሪያ ማውጣት ይታወሳል፡፡

በመሆኑም ንብረታችሁን ሳትሸጡ ኢትዮጵያ ውስጥ ትታችሁ የወጣችሁ ኤርትራውያን ንብረታችሁን ለማንቀሳቀስ ትችሉ ዘንድ ለዚሁ የተዘጋጀውን ፎርም በኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ኤምባሲ በግንባር ቀርቦ በመሙላት ማመልከት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

በለጠ መረጃ    Email: ethemb.community@telia.com

                    Tel.  +46 8 665 60 30 OR +46737245459  ማግኘት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

 

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ኤምባሲ

ስቶክሆልም

 

۞►◄►◊◄►◄►◊◄►◊►◄►◊◄►◄►◊◄►◄►◊◄►◄►◊►►◊◄►◄►◊◄►۞

 

ማስታወቂያ

መጋቢት 17 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም.

ጉዳዩ፡- የሚሌኒየም ቦንድ ሽያጭን በሀዋላ  ገንዘብ ማስተላለፍን ይመለከታል

በአካባቢያችን ያሉ ኢትዮጵያውያንና ትውልድ ኢትዮጵያውያን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን ቦንድ (EEPCo Millennium Bond) ሲገዙም ሆነ አካውንት መክፈት ሲፈልጉ ገንዘብ ወደ ሀገር ቤት በባንክ በኩል ወይም በሀዋላ ለማስተላለፍ የሚችሉ እንደሆነ መግለጻችን ይታወሳል፡፡

ይሁን እንጂ በሀዋላ ገንዘብ ለመላክ የፈለጉ ሰዎች ዌስተርን ዩኒየን የተባለው ገንዘብ መላኪያ ድርጅት የተቀባይ ስም (ገንዘቡ የሚላክለት ሰው ስም) ካልተገለፀ ተቀብዬ አልክም እያለ መሆኑ ስለተገለፀ ይህንኑ ችግር ለመቅረፍ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከድርጅቱ ጋር እየተወያየበት ይገኛል፡፡

በመሆኑም በውይይቱ እልባት እስኪገኝ ድረስ ግለሰቦች ገንዘቡን በባንክ በኩል እንዲልኩ እንዲገለጽላቸው እየጠየቅን፣ የቦንድ መግዢያ ገንዘቡን በሚልኩበት ጊዜ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የስዊፍት አድራሻ (SWIFT Address) CBETETAA መሆኑን፣ አካውንት መክፈትን በተመለከተ ይኸው አድራሻ እንደተጠበቀ ሆኖ ቅርንጫፍ ባንኮችን መጠቀም ከተፈለገ የራሳቸውን SWIFT አድራሻ (ለአራዳ ጊዮርጊስ ቅርንጫፍ፣ CBETETAAARA፣ ለፊንፊኔ ቅርንጫፍ CBETETAAFIN፣ ለጠመንጃ ያዥ ቅርንጫፍ CBETETAATEM፣ ለድሬዳዋ ቅርንጫፍ CBETETAADIR፣ ለሌሎች ቅርንጫፎችና ለኢንተርናሽናል ባንኪንግ ዲፓርትመንት CBETETAA) መጠቀም እንደሚገባ ይኸውም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና በኤምባሲያችን ዌብሳይት ላይ እንደሚገኝ እናስታውቃለን፡፡

በግንባር ባንክ ቀርበው ገንዘቡን በሚልኩ ጊዜ የመላኪያውን ዓይነት ሲመርጡ SWIFT የሚለውን መምረጥ እንደሚገባ እያሳሰብን ከዚህ ውጭ ያሉትን አማራጮች መጠቀም ግን ለአገልግሎት የሚፈፀመውን ክፍያ ሊያሳድገው እንደሚችልም እናስገነዝባለን፡፡

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ኤምባሲ

ስቶክሆልም

۞►◄►◊◄►◄►◊◄►◊►◄►◊◄►◄►◊◄►◄►◊◄►◄►◊◄►◄►◄►◄►◊◄►۞

 

ማስታወቂያ

መጋቢት 1ዐ ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም.

ጉዳዩ፡- የሚሌኒየም ቦንድ ሽያጭን ይመለከታል

 

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር በመተባበር በመንግሥት ሙሉ ዋስትና የተሰጠው የሚሌኒየም ቦንድ ሽያጭ እና የውጭ ምንዛሪ አካውንት መክፈት በውጭ ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልድ ኢትዮጵያውያን ማቅረቡ የሚታወስ ነው፡፡

በዚሁ መሠረትም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በአገር ውስጥ ከሚያከናውነው የቦንድ ሽያጭም ሆነ የውጭ ምንዛሪ አካውንት መክፈት ባሻገር በኤምባሲያዎች አማካይነት ለማከናወን ዝግጅቱን አጠናቋል፡፡

በመሆኑም የውጭ ምንዛሪ ባንክ አካውንት ለመክፈትም ሆነ የሚሌኒየም ቦንድ ለመግዛት የምትፈልጐ ኢትዮጵያውያንና ትውልድ ኢትዮጵያውያን በቀጥታ ከኤምባሲያችን ጋር ግንኙነት በማድረግ አገልግሎቱን ማግኘት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

 

ኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ኤምባሲ

ስቶክሆልም

۞►◄►◊◄►◄►◊◄►◊►◄►◊◄►◄►◊◄►◄►◊◄►◄►◊◄►◄►►◄►◊◄►۞

ማስታወቂያ

መጋቢት 1ዐ ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም.

ጉዳዩ፡- በሀገር ውስጥ የመኖሪያ ቤት መገንባትን ይመለከታል

 

በውጭ ሀገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በማህበር በመደራጀት በተለያዩ ክልሎች የመኖሪያ ቤት መስሪያ ቦታ እንዲያገኙ ለኤምባሲያችን ጥያቄዎች እያቀረቡ ድጋፍ ሲደረግ መቆየቱ ይታወሳል፡፡

በዚሁ መሠረት የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል በ2ዐዐ1 ዓ.ም. በውጭ ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልድ ኢትዮጵያውያን በሶዶ፣ በሆሣና፣ በወልቂጤ፣ በቡታጅራ፣ በወራቤ፣ በአላባ፣ በተርጫ እና በማሻ ከተሞች በውጭ ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልድ ኢትዮጵያውያን የመኖሪያ ቤት መስሪያ ቦታዎች ያዘጋጀ በመሆኑ በግልም ሆነ በማህበር በተጠቀሱት ከተሞች የመኖሪያ ቤት ለመስራት ፍላጐት ያላችሁ ለኤምባሲያችን በማመልከት የዕድሉ ተጠቃሚ መሆን የምትችሉ መሆኑን እያስታወቅን በተመሳሳይ መልኩ በቀጣይ በሌሎች ክልሎችም የሚኖረው የምናሳውቅ መሆኑን በዚሁ አጋጣሚ እንገልጻለን፡፡

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ኤምባሲ

ስቶክሆልም

۞►◊►◄►◊◄►◄►◊◄►◄►◊◄►◄►◊◄►◄►◊◄►◄►◊►►◊◄►◄►◊◄►۞
ማስታወቂያ

የካቲት 2ዐዐ1 ዓ.ም.

ጉዳዩ፡- የሚሌኒየም ቦንድ ሽያጭን ይመለከታል

 

በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልድ ኢትዮጵያውያን እራሳቸውን ጠቅመው ሀገራቸውን የሚጠቅሙባቸው በርካታ ስልቶችንና ፕሮግራሞችን መንግሥት በመቅረጽ ተግባራዊ ሲደርግ መቆየቱ ይታወቃል፡፡

ቀደም ሲል ሲያደርግ እንደቆየው ሁሉ መንግስት በውጭ ሀገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትዉልድ ኢትዮጵያውያን ተጠቃሚ ሆነው አገራቸውን እንዲጠቅሙ የሚያስችልና ቀደም ሲል ሲጠበቅ የነበረውን አዲሱ የሚሌኒየም ቦንድ ሽያጭ አዘጋጅቶ አቅርቧል፡፡

የሚሌኒየም የቦንድ ሽያጭ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽንና በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አማካይነት የተዘጋጀ ሲሆን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በውጭ ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልድ ኢትዮጵያውያን ሽያጩን ለማከናወን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሙሉ ኃላፊነቱን ወስዷል፡፡ የሀገሪቱን ኤሌክትሪክ (Universal electricity access) ፕሮግራም ለማሳካት የተዘጋጀው የኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን ሚሌኒየም ቦንድ የመንግስት ሙሉ ዋስትና ያለው ነው፡፡

በዚሁ መሠረት የሚሌኒየም ቦንዱ ዝቅተኛ መግዣ ዋጋ 5ዐዐ ዶላር ሲሆን ትውልድ ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያን ከዝቅተኛው ጣሪያ በላይ አቅማቸው የፈቀደውን ያህል መግዛት ይችላሉ፡፡

ከቦንድ ግዢው የሚገኝ ወለድ ለክፍያ የሚበቃበት ዝቅተኛ ጊዜ ገደብ አምስት አመት ሲሆን በዚሁ መሠረት ቦንዱን -

        ለ5 ዓመት የሚገዙ 4 በመቶ ወለድ

        ለ7 ዓመት የሚገዙ 4.5 በመቶ ወለድ

        ለ1ዐ ዓመት የሚገዙ 5 በመቶ ወለድ የሚያስገኝ ነው፡፡

ከቦንድ ግዢው የሚገኝ ገቢ ከማንኛውም ገቢ ግብር ነፃ ሲሆን በመንግስትም ሙሉ ዋስትና የተሰጠው ነው፡፡

በመሆኑም በስዊድንና በአካባቢው የምትኖሩ ኢትዮጵያውያን የቦንዱ ሽያጭ የተጀመሪ በመሆኑ በዚህ እድል ተጠቃሚ ለመሆን የምትፈልጉ ኢትዮጵያውያንና ትውልድ ኢትዮጵያውያን በቀጥታ ማንኛውንም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፎች በስልክ ወይም በፋክስ ግንኙነት በማድረግ ክፍያውን በመፈፀም ቦንዱን መግዛት የምትችሉ መሆኑን እናስታውቃለን፡፡

ለበለጠ መረጃ ኤምባሲያችንን ኮንታክት ማድረግ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

የኢትዮጵያ ኤምባሲ

ስቶክሆልም


۞►◊►◄►◊◄►◄►◊◄►◄►◊◄►◄►◄►◄►◊◄►◄►◊►►◊◄►◄►◊◄►۞

ማስታወቂያ

ጥር 28 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም.

ጉዳዩ፡- ታላቅ የጠረጴዛ ዙሪያ ዓለምአቀፍ የኢኮኖሚ ኮንፈረንስ በኢትዮጵያ

በአፍሪካ የመጀመሪያ የሆነው ዓለምአቀፍ የጠረጴዛ ዙሪያ የቢዝነስ እና ኢኮኖሚ ኮንፈረንስ በኢትዮጵያ እ.ኤ.አ. ማርች 23 እና 24 ቀን 2ዐዐ9 ዓ.ም. ይካሄዳል፡፡

ጉባዔው ከሰሃራ በታች ዓለምአቀፍ ትኩረትን እየሳበ በመጣው በኢትዮጵያ የቢዝነስ፣ የቱሪዝም ኢንቨስትመንት፣ ንግድ እና በአጠቃላይ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ አማራጮችና እድሎች ዙሪያ ይወያያል፡፡

የኢትዮጵያ አማራጭ የኢንቨስትመንት እድሎች እና ችግሮች ዙሪያ፡-

        የኢትዮጵያ የአጭርና የረዥም ጊዜ የቢዝነስ ራዕዮች ምንድናቸው?

        በቀጣይ ዓመታት ኢትዮጵያ እራሷን የምሥራቅ አፍሪካ የቢዝነስ ማዕከል ማድረግ ትችላለችን?

        የኢትዮጵያን እምቅ የቱሪዝም ሃብት እንዴት ለዓለም የቱሪዝም ገበያ ውስጥ እንዴት ሊገባ ይችላል? እንዴትስ ለዓለምአቀፍ የቱሪዝም ገበያ በይበልጥ ክፍት ማድረግ ይቻላል?

        በቢዝነስ ዙሪያ ያሉ የሙስናና የመሠረተ-ልማት ችግሮችን እንዴት ማስወገድ ይቻላል? የሚሉና ሌሎችም ጥያቄዎች ተነስተው በሰፊው ይተነተናሉ፡፡

በጉባዔው ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊን ጨምሮ ሌሎች ሁሉም የሚመለከታቸው ሚኒስትሮችና ታዋቂ ኢኮኖሚስቶችና ባለሙያዎች በጥያቄዎቹ ዙሪያ ማብራሪያዎችን ይሰጣሉ፡፡

ኮንፈረንሱ የኢትዮጵያውያን የቢዝነስ ተቋማት እርስ በርስም ሆነ ከሌሎች የቢዝነስና ኢኮኖሚ ተቋማት ጋር ኔትዎርክ እንዲፈጥሩ ሰፊ የግንኙነት መድረክ የመክፈት ዓላማም ያለው ነው፡፡

በመሆኑም በዚህ ታላቅ የኢኮኖሚ ኮንፈረንስ ላይ ለመሳተፍ የምትፈልጉ ምዝገባ በኢንተርኔት በመከናወን ላይ በመሆኑ ከወዲሁ እንድትመዘገቡ እናሳስባለን፡፡

በኢንተርኔት ለመመዝገብ የምትፈልጉ የምዝገባ ቅጹን ከኤምባሲው ዌብሣይት www.ethemb.se ላይ ማግኘት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ኤምባሲ

ስቶክሆልም
 

۞►◊►◄►◊◄►◄►◊◄►◄►◊◄►◄►◊◄►◄►◊◄►◄►◊►►◊◄►◄►◊◄►۞

ማስታወቂያ

ጥር 28 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም.

በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልድ ኢትዮጵያውያን በአገራችን ልማት እንዲሳተፉና ከትውልድ አገራቸው ጋር የጠበቀ ሕብረት እንዲኖራቸው ለማስቻል መንግሥት የተለያዩ ተግባራትን እያከናወነ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ከነዚህም ሥራዎች መካከል አንዱ በውጭ የሚኖሩ ማህበረሰብ አባላት ገንዘባቸውን በሕጋዊ መንገድ ወደ አገር ቤት ማስተላለፍና በአገር ውስጥ ባንኮች ማስቀመጥ እንዲችሉ ማድረጉ ተጠቃሽ ነው፡፡

በዚህ መሠረት በውጭ የሚኖረው ማህበረሰብ የውጭ ምንዛሪ አካውንት መክፈት የሚቻልባቸው ባንኰች፣ ገንዘብ ወደ አገር ቤት ለማስተላለፍ የሚያስችሉ የገንዘብ አስተላላፊ ተቋማትና የሚያስከፍሉትን ዋጋ በተመለከተ አዲስ የወጣ መረጃ በኤምባሲያችን ድረ-ገጽ www.ethemb.se ላይ ማግኘት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ኤምባሲ

ስቶክሆልም

 

۞►◊►◄►◊◄►◄►◊◄►◄►◊◄►◄►◄►◊◄►◄►◊◄►◄►◊►►◊◄►◄►◊◄►۞

ማስታወቂያ

ጥቅምት 18 ቀን 2001 ዓ.ም

ጉዳዩ፡- በሀገር ውስጥ ባንኮች የውጭ ምንዛሪ ሂሳብ መክፈት ስላሚቻልበት

     በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልድ ኢትዮጵያውያን በትውልድ ሀገራቸው ውስጥ በሚገኙ ባንኮች በውጭ ምንዛሪ አካውንት መክፈት እንዲችሉ በወጣው መመሪያ መሰረት አመልካቾች በኢትዮጵያ ንግድ ባንኮች የውጭ ምንዛሪ አካውንት እንዲከፍቱ ሲደረግ መቆየቱ ይታወሳል፡፡

     ይሁን እንጂ በአሁኑ ወቅት ከንግድ ባንኮች በተጨማሪ አንበሳ ኢነተርናሽናል ባንክ፤ አቢሲኒያ ባንኮችን ቅርንጫፎቻቸው በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልድ ኢትዮጵያውያን የውጭ ምንዛሪ አካውንት መክፈት የሚቻሉበትን ሁኔታዎች አመቻችተዋል፡፡

     በመሆኑም በእነዚህ ባንኮች በግልም ሆነ በጋራ የውጭ ምንዛሪ አካውንት ለመክፈት የምትፈልጉ ኢትዮጵያውያንና ትውልድ ኢትዮጵያውያን የሚቦሉ ፎርሞችንም ሆነ ሌሎች ተጨማሪ መርጃዎችን ከኤምባሲው ወይም ከኢምባሲው ድረ-ገፅ http://www.ethemb.se/ee_community.html ማግኘት የምትችሉና የአገልግሎቱ ተጠቃሚ መሆን የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

የኢትዮጵያ ኤምባሲ

ስቶክሆልም

 

۞◄►◄►◊◄►◊◄►◄►◊◄►◄►◊◄►◄►◄►◊◄►◄►◊◄►◄►◊◄►◄►◊►۞

ማስታወቂያ

                             ሐምሌ 9 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም.

በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ትውልድ ኢትዮጵያውያን ለሀገራቸው ልማት አስተዋጽኦ ማድረግ ስለሚችሉበት ሁኔታ የኢትዮጵያ ሚሌኒየም ለማክበር ወደ ሀገራቸው ሄደው ከነበሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልድ ኢትዮጵያውያን ጋር ውይይት መደረጉ የሚታወስ ነው፡፡

በዚሁ ወቅት በሀገር ውስጥ ከውጭ ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የሚፈለጉ የእውቀት፣ የማቴሪያል፣ የፋይናንስና ሌሎች ፍላጐቶች በዝርዝር ተለይተው እንዲገለጹ በውጭ በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በቀረበው ጥያቄ መሠረት የተለያዩ መ/ቤቶች ከውጭ ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ወገኖች የሚፈልጓቸውን የድጋፍ ትብብር አይነቶች አዘጋጅተው ለኤምባሲያችን በመላክ ላይ ናቸው፡፡

በመሆኑም የሚፈለጉ የድጋፍ አይነቶችን ከኤምባሲያችን ዌይሣይት ላይ በመመልከት ለሀገራችሁ ልማትና እድገት የበኩላችሁን ድጋፍ በማድረግ የሀገራችሁ ልማት አጋዥ እንድትሆኑ በአክብሮት የተጋበዛችሁ መሆኑን እንገልጻለን፡፡ 

ዝርዝሩን ለመመልከት ይህን ይጫኑ

የኢትዮጵያ ኤምባሲ

ስቶክሆልም

 

۞◄►◄►◊◄►◊◄►◄►◊◄►◄►◊◄►◄►◄►◊◄►◄►◊◄►◄►◊◄►◄►◊►۞

 

                              ግንቦት 26 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም.

ማስታወቂያ

በውጭ ሀገር ለተገኙ የትምህርት ማስረጃዎች አቻ ግምት ለመስጠት ማስረጃዎቹ በተገኙበት ሀገር የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ትክክለኛነታቸው የተረጋገጠ መሆን ያለበት ቢሆንም በውጭ ሀገር ተምረው የሚመለሱ ተማሪዎችና የአገልግሎቱ ጠያቂዎች ይህን ባለመገንዘብ የትምህርት ማስረጃቸው አቻ ግምት እንዲሰጣቸው እየጠየቁ ነው፡፡

በመሆኑ አገልግሎቱን በተገቢው መንገድ ለመስጠትና ሕጋዊ ያልሆኑ ዶክመንቶችን ለመለየት በውጭ ሀገር ትምህርታችሁን አጠናቃችሁ ስትመለሱ የትምህርት መረጃዎቻችሁን በተማራችሁበት ሀገር የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር  እንድታረጋግጡ የትምህርት ሚኒስቴር መመሪያ ያስተላለፈ መሆኑን እናስታውቃለን፡፡

የኢትዮጵያ ኤምባሲ

ስቶክሆልም

 

۞◄►◄►◊◄►◊◄►◄►◊◄►◄►◊◄►◄►◊◄►◄►◊◄►◊◄►◄►◊◄►◄►◊►۞

ማስታወቂያ

ሰኔ 27 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም.

 በግል የመኖሪያ ቤት የቦታ ጥያቄ አመልካቾች

የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በግልና በማህበር በመደራጀት የመኖሪያ ቤት ለመስራት እንዲችሉ ባወጣው የቦታ አሰጣጥ መመሪያ መሠረት የሚቀርቡ ጥያቄዎችን በስፋት እያስተናገደ እንደሚገኝ ይታወቃል፡፡

በክልሉ በአሁኑ ወቅት በአዲስ አበባ ዙሪያ እስከ 1ዐዐ ማይልስ ድረስ በሚገኙ ከተሞች ለመኖሪያ ቤት የተዘጋጀ ቦታ በመጠናቀቁ አነዚህን ከተሞች በሚመለከት የሚቀርቡ የቦታ ጥያቄዎችን ማስተናገድ መቆሙን የክልሉ በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ጉዳዮች ማስተባበሪያ ቢሮ ሰኔ 26 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም. ለኤምባሲያችን በጻፈው ደብዳቤ በመግለጽ ይኸው ለማህበረሰቡ እንዲተላለፍ ጠይቋል፡፡

ስለሆነም በኦሮሚያ ክልል በአዲስ አበባ ከተማ ዙሪያ እስከ 1ዐዐ ማይልስ ድረስ ባሉት ከተሞች ለመኖሪያ ቤት የተዘጋጀ ቦታ ለጊዜው የሌለ መሆኑ ታውቆ የቦታ ዝግጅት እስኪደረግ ድረስ የሚቀርቡ የቦታ ጥያቄዎችን ከ1ዐዐ ማይልስ ክልል ውጭ ባለው ክልል ውስጥ የሚስተናገዱ መሆኑን እናስተውቃለን፡፡

የኢትዮጵያ ኤምባሲ

ስቶክሆልም

۞◄►◊◄►◊◄►◄►◊◄►◄►◊◄►◄►◊►◄►◊◄►◄►◊◄►◄►◊◄►◄►◊►۞

 

Ñ

 

ሌሎች ማስታወቂያዎች

 

Ethiopian Heroes in Athletics

Abebe Bikila. Gold medal 1960 Olympics

Ethiopia's 1968 Olympic Marathon champion Mamo Wolde

Shaleka Deratu Tulu

 

 

 

 

www.ethemb.se Box 10148 100 55 Stockholm  /  Tel. +46-8-665 60 30 / Fax. +46-8-6608177 /  Email. ethemb.community@telia.com,  public.ethemb@yahoo.com