የታላቁ ህዳሴ ግድብ ቦንድ ማብራሪያ
ሰነድ
ቦንዱን በመግዛት በታላቁ የኢትዮጰያ
የህዳሴ ግድብ ግንባታ አሻራዎን ያኑሩ!
የኢትዮጵያ መንግሥት በአባይ ወንዝ ላይ ታላቁን የህዳሴ ግድብ ለመገንባት በቁርጠኝነት ተነሳስቷል:: ይህን
ግንባታ ለማከናወን የሚያስፈልገው የፋይናንስ መጠን ከፍተኛ ሲሆን ይሄንኑ ገንዘብም ሙሉ በሙሉ ከሀገሪቱ
ተወላጆች ለማሰባሰብ ታቅዷል፡፡ በመሆኑም የሚፈለገውን ገንዘብ በቁጠባ መልክ ለማሰባሰብ እንዲቻል የህዳሴ
ግድብ ቦንድ ለሽያጭ ቀርቧል፡፡
የቦንዱ ምንነት
እንደ ፕሮሚሰሪ ኖት ወይም የግምጃ ቤት ሰነድ የብድር (የዕዳ) ሰነድ ነው፡፡
የህዳሴ ግድብ ቦንድ ጠቀሜታዎች
ለአገር
ያለው ጠቀሜታ፡-
ውጭ አገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትየጵያውያን ካላቸው ገቢ በመቆጠብ ለሀገራቸው ልማት
የሚያስፈለገውን የውጭ ምንዛሪ ግኝትን በማሳደግ ለራሳቸው ተጠቅመው አገራቸውን እንዲጠቅሙ ያስችላቸዋል፣
3.1.
ለገዢዎች ያለው ጠቀሜታ፡-
-
ቦንድ ገዥው ከገቢው በየጊዜው ገንዘብ እንዲቆጥብ በማድረግ ሀብት እንዲፈጥር ያደርገዋል፣
-
ከቦንድ ግዢ የሚገኘው የወለድ ገቢ ከቀረጥ ነፃ ነው፣
-
ቦንዱን ለገዢው ሕጋዊ ወራሾች እንዲሁም ለሌላ ሁለተኛ ወገን በውርስና በስጦታ ማስተላለፍ ይቻላል፣
ቦንዱን በሁለተኛ ገበያ (secondary market) ለሌላ ሰው ወይንም ድርጅት መሸጥ ይቻላል፣
እንዲሁም ቦንዱን በዋስትና አሲይዞ ከሀገር ውስጥ ባንክ ገንዘብ