የትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርድ/

Ethiopian Origin ID

 

ትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርድ መVላት ያለባቸው

01. ለአዲስ የትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርድ

  1. በሁለት ኮፒ በሚገባ ተሞልቶ የተፈረመ የአዲስ ትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርድ ማመልከቻ ቅፅ /001 ወይም 002 ቅጹን በሁለት ኮፒ ይሙሉ/፣

  2. በቅርብ ጊዜ የተነሳና ሙሉ ፊትን የሚያሣይ 3x4 የሆኑ 3 ፎቶግራፎች ከማመልከቻ ቅጽ ጋር ያያይዙ፣

  3. ከቅጹ ጋር ኢትዮጵያዊ ተወላጅ መሆንዎን የሚያረጋግጥ ሰነድ ዋናውንና ከየዓይነቱ ሁለት ኮፒ ያያይዙ፣

  4. ዜግነት ከወሰዱበት ሀገር አግባብ ካለው አካል የፀና ኦሪጅናል ፓስፖርት እና በአገሩ የተመዘገቡበትን ሰነድ /Personbevis-Sweden, Folkeregister-Denmark, Folkeregister-Norway, Extrat from the Population Information System-Finland, Einstaklingar-Iceland/ ያቅርቡ፣/ ሪጅናል ፓስፖርትዎን ይላኩ/

  5. መታወቂያውን ለመውሰድ በአካል ቀርበው ለሚያመለክቱ 5ዐዐ.ዐዐ የአሜሪካን ዶላር ወይም ክፍያውን በኤምባሲው PlusGirot ባንክ የሚፈፅሙ ከሆነ 5ዐዐዐ.ዐዐ የስዊድን ክሮነር የሚያስፈልግ ሲሆን ክፍያው በ/IBAN No.  SE62 9500 0099 6026 0629 2478, SWIFT-Code NDEASESS, ወይም PlusGirot  No. 629247-8./ መፈፀም ይኖርበታል፡፡ እንዲሁም ለባንክ ኮሚሽን 60 ክሮነር እና የፖስታ መልሶ መላኪያ 100 ክሮነር ተጨማሪ ክፍያ ማስተላለፍ ይጠበቅባቸዋል፡፡

      ክፍያን በፖስታ መላክ አይቻልም፡፡

  6. ሚጠይቁት መታወቂያ በጋብቻ ከሆነ እንደአግባብነቱ ጋብቻው ለት ዓመት የፀና መሆኑን የሚያሳይ ማረጋገጫ ሰነድና የአመልካቹ/ቿ ባል/ሚስት ያወጣውን/ያወጣችውን የኢትዮጵያ ተወላጅ መታወቂያ ካርድ ወይም በአገልግሎት ላይ ያለ የኢትዮጵያ ፓስፖርት  በማያያዝ ያቅርቡ፣

  • አስራ ስምንት ዓመት ያልሞላቸው ልጆችዎን የልደት የምስክር ወረቀት ወይም ተመሳሳይ መረጃ በማቅረብ በወላጅ መታወቂያ ላይ በማስመዝገብና በልጆቹ ፓስፖርት ላይ የኢትዮጵያ ተወላጅ ማህተም በማስደረግ የተለያዩ አገልግሎቶችን እንዲያገኙ ያስችላቸዋል::

/ አስራ ስምንት ዓመት ያልሞላቸው ልጆችዎን  ኦሪጅናል ፓስፖርት ይላኩ/

የኢትዮጵያ ተወላጅ መታወቂያ ካርድ የመጠየቂያ ቅጽ አሞላል ማብራሪያ

1. ጾቹ በሙሉ የሚሞሉት በራሱ በአመልካቹ ብቻ ይሆናል፡፡

1.  ቅጾቹን በጥንቃቄና በግልጽ ይሙሉ፣

2.  በቅጾቹ ላይ የአመልካች ሙሉ ስም በአማርኛና በእንግሊዝኛ ቋንቋዎች ይሞሉ፣

3.  ከስም በስተቀር የቅጹን ቀሪ ክፍል አመልካች በመረጡት በእንግሊዝኛ ወይም በአማርኛ ቋንቋ መሙላት ይችላሉ፣

4.  በቅጹ ላይ መሞላት ያለበት ቀን፣ ወር፣ ዓመተ ምህረት (ዘመን) አመልካች በኢትዮጵያ ወይንም እ.ኤ.አ. መርጠው መሙላት ይችላሉ፡፡ ሆኖም በሰነድ ላይ የሚታይ ከሆነ በሰነዱ ላይ በተጻፈበት የዘመን አቆጣጠር ይጠቀሙ፣

 

02. ትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርድ እድሳት

  •   በሁለት ኮፒ በሚገባ ተሞልቶ የተፈረመ ትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርድ የእድሳት ማመልከቻ ቅፅ /003  በሁለት ኮፒ ይሙሉ/፣

  •     በቅርብ ጊዜ የተነሳና ሙሉ ፊትን የሚያሣይ 3x4 የሆኑ 2 ፎቶግራፎች ከማመልከቻ ቅጽ ጋር ያያይዙ፣

  •    ዜግነት ከወሰዱበት ሀገር አግባብ ካለው አካል የተሰጠና የፀና ኦሪጅናል ፓስፖርት እና በአገሩ የተመዘገቡበትን ሰነድ /Personbevis-Sweden, Folkeregister-Denmark, Folkeregister-Norway, Extrat from the Population Information System-Finland, Einstaklingar-Iceland/ ያቅርቡ፣/ ሪጅናል ፓስፖርትዎን ይላኩ/

ማስታወሻ፡-

 በስዊድን ነዋሪ የሆኑ የተዘጋጀላቸውን የትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርድ የመመለሻ አድራሻ በግልፅ የተፃፈበትና ባለ 61 ክሮነር ስታምፕ/ቴምብር የተለጠፈበት ፖስታ አብሮ መላክ፣

 ከስዊድን ውጭ የሚኖሩ የተዘጋጀላቸውን የትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርድ መመለሻ አድራሻ በግልፅ የተፃፈበት ፖስታና  የ1ዐዐ ክሮነር የተመጣጣኝ የሆነ ዋጋ ያለው ኢንተርናሽናል ኩፖን መላክ ይኖርባቸዋል፡፡

ኤምባሲው ለአገልግሎቱ ከሚጠይቀው የክፍያ መጠን እንዲሁም የባንክ ኮሚሽንና የፖስታ መላኪያ ገንዘብ ውጭ የሚፈፀም ማንኛውም በትርፍ ገቢ የሆነ ገንዘብ የማይመለስ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

 

ማመልከቻ ቅጾቸች

 Application Forms

 

 

01. ለአዲስ የትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርድ ማመልከቻ ቅፅ

01. For New Ethiopian Origin ID Application Form

 

001 (PDF)

(For Ethiopian Origins)

 

002 (PDF)

(For Foriegn National Spouse)

 

 

02. ትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርድ እድሳት ቅፅ

Ethiopian Origin ID Renewal Form

003. (PDF)

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

Postal Address

Embassy of the Federal Democratic Republic of Ethiopia

P. O. Box 10148

100 55 STOCKHOLM, SWEDEN

 

Telephone

+46-8-6656030 (Ext.6)

13:30 - 15:30 Hrs.

 

Visiting Address

Embassy of Ethiopia

Löjtnantsgatan 17

115 50 STOCKHOLM

 

9:00 - 12:00 Hrs. (Visiting hours) 

Tel. 46 8 665 60 30