|
የውክልና ሰነድ ለማረጋገጥ መሟላት የሚገባቸው ሰነዶች
ማስታወሻ:-
1)
የሚረጋገጠው ሰነድ የኢትዮጵያዊ ወይም የኢትዮጵያ ተወላጅ ከሆነ፡-
§
በግንባር ኤምባሲው በመምጣት ለሚጠየቅ የውክልና አገልግሎት ወካይ በቆንስላ
ኃላፊ ወይም ከቆንስላ ክፍል ሠራተኛ ፊት አገልግሎት ላይ ያለ የኢትዮጵያ ፓስፖርት ወይም
Allen's or Travel document
የኢትዮጵያ ተወላጅ መታወቂያ ካርድ ይዞ በመቅረብ በውክልና ሰነዱ ላይ መፈረም፣
§
በፓስታ ቤት በኩል የመጣ ከሆነ እንዲረጋገጥ በቀረበው ሰነድ ላይ ወካይ
ፊርማውን በሚኖርበት አካባቢ ጠበቃ ፊት በመቅረብ መረጋገጡንና የወካዩን ማንነት የሚያሳይ አገልግሎት
ላይ ያለ ፓስፖርት ወይም የኢትዮጵያ ተወላጅ መታወቂያ ካርድ ማቅረብ፣
§
ከሚኖሩበት ሀገር ከፖሊስ ወይም ከኢሚግሬሽን የተሰጠ የማንነት መታወቂያ
(
ከስዊድን Personbevis, ከዴንማርክ
Folkeregisteret, ከኖርዌይ
Folkeregister, ከፊንላንድ
Extract from the Population Information System,
ከአይስላንድ
Einstaklingar'
ወይም A paper from Police or Immigration Authority)
§
ክፍያ፡-
ü
ሰርተፊኬት ነክ (የልደት የምስክር ወረቀት፣ የጋብቻ የምስክር ወረቀት፣
የትምህርት የምስክር ወረቀት፣ የመንጃ ፈቃድ ወዘተ...) ከሆነ
49ዐ ክሮነር፣
ü
ከላይ ከተጠቀሱት ሰነዶች ውጪ ለሚቀርብ ማንኛውም ማመልከቻ
515 ክሮነር፣
§
በውክልና ሰነዱ ላይ የወካይና የተወካይ ሙሉ ስም፣ የፓስፖርት ቁጥር፣ ዜግነት፣
የትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርድ ቁጥር እና አድራሻ፣
§
ማስታወሻ፡-
ü
የሚረጋገጠው ዋናው ሰነድ (Original Document) መላክ ይኖርበታል፡፡
ü
ክፍያ የሚፈፀመው ለእያንዳንዱ ፊርማ ነው፡፡
2)
የውጭ ሃገር ዜግነት ባላቸው አመልካቾች ለሚቀርብ ሰነድ፡-
§
በጠበቃና በአገሩ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጋገጡንና ከአሁን በፊት የተረጋገጠ
ከሆነም ከአንድ ዓመት ያልበለጠው መሆን ይኖርበታል፣
§
ክፍያ፡-
ü
ለልደት፣ ለጋብቻና የትምህርት ሰርተፊኬት 747 ክሮነር ሲሆን ሌሎች ሰነዶች
790 ክሮነር፣
3)
ከኢትዮጵያ የመጣን
ማንኛውም ሰነድ ለማረጋገጥ በቅድሚያ፡-
§
በኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጋገጥ
ይኖርበታል፣
§
ከአሁን በፊት የተረጋገጠ ከሆነም ከአንድ ዓመት ያልበለጠው መሆን ይኖርበታል፣
§
ጊዜው ያላለፈበት ኦሪጂናል ፓስፖርትና ኮፒ ይዞ መቅረብ/
በፖስታ የሚላክ ከሆነም የፓስፖርት
ኮፒው ትክክለኛ
ኮፒ መሆኑ አመልካች በሚኖርበት ሀገር ጠበቃ መረጋገጥ ይኖርበታል፡፡
ከስዊድን ውጭ ላሉ አመልካቾች
§ ከሰነዱ ማረጋገጫ ክፍያ በተጨማሪ 68 ክሮነር ለባንክ ኮሚሽን፣ ለፖስታ መላኪያ
1ዐዐ ክሮነር (ሰነዱን መልሶ መላኪያ) ክፍያውንም
Nordea Bank
IBAN
No. SE62 9500 0099 6026 0629 2478,
SWIFT-Code NDEASESS,
OR
Postgiro
No. 629247-8 መፈፀም፣
§
የተቀባይ አድራሻ ያለበት ቴምብርና ፖስታ ከተላከ ለፖስታ መላኪያ ክፍያ
አያስፈልግም፡፡
§
የተፈፀመ ትርፍ ክፍያ አይመለስም፡፡
የውክልና መስጫ ቅፅ
(pdf)
ቀደም ሲል የተሰጠን ውክልና ለማንሳት/ ለመሻር
አጠቃላይ ሂደቱ እና መምዋላት የሚገባቸው ቅድመ ሁኔታዎች ውክልና ለመስጠት
ከሚያስፈልገው ጋር ተመሳሳይ ነው፡፡
ውክልና ማንሻ ቅፅ (PDF)
የፖስታ መላኪያ ክፍያን በሚመለከት
ከስዊድን ለሚቀርቡ ማመልከቻዎች
አመልካቾች
-
እስከ 100 ግራም ክብደት ላለው ሰነድ የ68 የስዊድን ክሮነር ቴምብር
-
እስከ 250 ግራም ክብደት ላለው ሰነድ የ72 የስዊድን ክሮነር ቴምብር
-
እስከ 500 ግራም ክብደት ላለው ሰነድ የ83 የስዊድን ክሮነር ቴምብር እንዲሁም እስከ
1000 ግራም ክብደት ላለው ሰነድ የ94 የስዊድን ክሮነር ቴምብር የተለጠፈበት እና
የተቀባይ ሙሉ አድራሻ በትክክል የተፃፈበት ፖስታ
(envelop)
መላክ ይኖርባቸዋል፡፡
ከስዊድን ውጭ ለሚቀርቡ ማመልከቻዎች
Postal Address
Embassy of the
Federal Democratic Republic of Ethiopia
P. O. Box 10148
100 55 STOCKHOLM, SWEDEN
E-mail:-
ethemb.consular@telia.com
|