VISA AND OTHER CONSULAR MATTERS

Visa  |  Passport   Ethiopian Origin ID   Certificate of National Identity   |  Laissez Passer   Legalisation   Duty and Duty Free

 

ለፓስፖርት የሚቀርቡ ማመልከቻዎች / Application For Passport Issues  

 

Before start to complete passport application form and send your application documents, download the following application kit and read the instruction guide carefully.     

Please read this Kit =>  Passport Application Kit

Read also the following checklists.

 

 1.1  ለአዲስ ፣ ለቅያሬ ለእድሳት ወይም በጠፋ ምትክ ለሚሰጥ የሚቀርብ ማመልከቻ

  1. በሚገባ የተሞላ checklist ፎርም (በ2 ኮፒ)

  2. የፓስፖርት ማመልከቻ ቅጽ (በ2 ኮፒ) በአማርኛና በእንግሊዝኛ በሙሉ በሙሉ የተሞላ፣ 

  3. የኢትዮጵያዊነት ማረጋገጫ ሰንድ (የቀድሞ ፓስፖርት፣ የልደት ወረቀት፣ መንጃ ፈቃድ፣ የመስሪያ ቤት መታወቂያና ሌሎች ማንነትን የሚገልፁ ሰነዶች ዋናውና ቅጂው)(ዋናው ከ2 ፎቶ ኮፒ ጋር)

    • ፓስፖርት ውጭ የሚቀርብ ማንኛውም የኢትዮጵያዊነት ማረጋገጫ ሰንድ በኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ትክክለኛነቱ የተረጋገጠ መሆን ይኖርበታል፡፡

    • በምስክር የሚቀርብ ምንም አይነት ማመልከቻ ተቀባይነት የለውም፡፡

  4. ከሚኖሩበት ሀገር ኢሚግሬሽን ወይም ስነ ህዝብ ምዝገባ ፅ/ቤት ወይም ከፖሊስ የተሰጠ የምዝገባ ሰነድ (ኢትዮጵያዊ ዜግነትን በሚያሳይ መልኩ)(በ2 ኮፒ)

  • (ከስዊድን Personbevis,

  • ከዴንማርክ Folkeregisteret,   

  • ከኖርዌይ Folkeregister, 

  • ከፊንላንድ Extract from the Population Information System,

  • ከአይስላንድ Einstaklingar' ወይም A paper from Police or Immigration Authority)፣

  • በስተቀኝ በኩል ለማሳያ የተቀመጡ ናሙናዎችን ይመልከቱ፡፡

5. የፖሊስ ማስረጃ (Police clearance) (*በጠፋ ምትክ ለሚቀርብ የፓስፖርት ማመልከቻ)

6. የጣት አሻራ ቀደም ሲል የጣት አሻራ በመስጠት አዲሱን ማሽን ሪደብል ፓስፖርት ካወጡ አመልካቾችና እድሜው ከ14 አመት በታች ከሆኑ ህፃናት በስተቀር ሌሎች የፓስፖርት አመልካቾች ለአዲስ፣ ለእድሳት ወይም ለቅያሬ የጣት አሻራ መስጥት ይኖርባቸዋል፡፡

  • የግራና የቀኝ እጅ አመልካች ጣቶች (right hand-index finger (Fingercode 07) and left hand -index finger (Finger code 02)) አሻራ በሚገባ በጣት አሻራ ፎርም ላይ መስጠት ይኖርበታል፡፡

  • በጣት አሻራ መስጫ ፎርሙ ላይ አመልካች ስሙን፣ አሻራ የሰጠበትን ቀን፣ ፊርማውንና አሻራው የተወሰደበትና የጣት ኮድ (Finger Code) ብቻ ማስቀመጥ ይኖርበታል፣ ቀሪው በኮንሱላር ሰራተኛ የሚሞላ ይሆናል፡፡   

  • በግንባር ቀርበው የሚያመለክቱ ጣት አሻራ በኤምባሲው ሊሰጡ ይችላሉ፡፡ የጣት አሻራ በኤምባሲው ለመስጠት ቀጠሮ መያዝ አያስፈልግም፡፡

  • በግንባር መቅረብ የማይችሉ በሚኖሩበት አካባቢ በሚገኝ ፖሊስ ወይም ጠበቃ ፈት ቀርበው መስጠት ይኖርባቸዋል፡፡ (*የተሰጠው አሻራ የአመልካቹ ስለመሆኑ በጣት አሻራ ተቀባዩ አካል ወይም ተቋም መረጋገጥ ይኖርበታል፡፡ ወይም ይህንኑ የሚገልፅ/የሚያረጋግጥ ማህተም ወይም ጽሑፍ ሊኖርበት ይገባል)፡፡ ይህ ካልሆነ የጣት አሻራው ተቀባይነት አይኖረውም፡፡

7. ሶስት (3) ፎቶግራፍ (መጠኑ 3x4 cm የሆነና ከ6 ወር ያልበለጠው ስለመሆኑ )፣ የፎቶውን ይዘት ዝርዝር ከታች ይመልከቱ፣

8. ክፍያ መፈፀምና ክፍያ የተፈፀመበትን ደረሰኝ ከማመልከቻው ጋር አያይዞ ማቅረብ፣ (*በግንባር ቀርበው የሚያመለክቱ በካሽ መክፈል ይችላሉ)፣ የክፍያውን አፈፃፀም ይዘት ከታች ይመልከቱ፣

9. ባዶ ፖስታ (*በአካል ቀርበው ለማይረከቡ አመልካቾች ፓስፖርቱ ከተሰራ በኋላ ተመልሶ የሚላክበት የአመልካች የፖስታ አድራሻ የተፃፈበትና በቂ መላኪያ ቴምብር የተለጠፈበት ወይም ኮፖን የተያያዘበት ባዶ ፖስታ መላክ ያስፈልጋል፣ የፖስታ አላላክን በተመለከተ ከታች ያለውን ማብራሪያ ይመልከቱ

 

1.2 በውጭ ሃገር ለተወለዱ (*ከ14 አመት በታች ያሉ) ሕፃናት አዲስ ፓስፖርት ማመልከቻ

  1. በሚገባ የተሞላ CHECKLIST ፎርም፣

  2. የፓስፖርት ማመልከቻ ቅጽ በሁለት ቅጂ

  3. ምዝገባ ሰነድ (ከሚኖሩበት ሀገር ከኢሚግሬሽን፣ ከስነ ህዝብ ምዝገባ ፅ/ቤት የተሰጠ (ዜግነትን በሚያሳይ መልኩ) የምዝገባ ሰነድ)

  4. የወላጅ ፓስፖርት ኮፒ

  5. የልጅ ልደት ሰርተፍኬት፣ (ከኢሚግሬሽን ወይም ከፖሊስ የተሰጠ የምዝገባ ሰነድ ወይም የማንነት (ዜግነትን በሚያሳይ መልኩ) ማረጋገጫ ወረቀት)

  6. የልጅ ማስመዝገቢያ ቅፅ (*በወላጆች በሚገባ ተሞልቶ የተፈረመ)፣

  7. አራት ፎቶግራፍ (መጠኑ 3x4 cm የሆነ)

  8. ከሚኖሩበት ሀገር የቤተሰብ ምዝገባ (Family Registration) ተያይዟል፣ (በውጭ ሃገር ለተወለዱ ሕፃናት) (ከስዊድን Family Personbevis, ከዴንማርክ Family Folkeregisteret, ከኖርዌይ  Bostedsattest (Family), ከፊንላንድ Family Extract from the Population Information System, ከአይስላንድ Einstaklingar' ወይም A Family Registration paper from Population registration office or Immigration Authority)፣

  9. በቂ ክፍያ መፈጸምና ክፍያ መፈፀምና ክፍያ የተፈፀመበትን ደረሰኝ ከማመልከቻው ጋር ማያይዝ

  10. ተመልሶ የሚላክበት ባዶ ፖስታ (*በአካል ቀርበው ለማይረከቡ አመልካቾች ፓስፖርቱ ከተሰራ በኋላ ተመልሶ የሚላክበትና የአመልካች አድራሻ የተፃፈበት፣ በቂ መላኪያ ክፍያ የተከፈለበት ባዶ ፖስታ፣ የፖስታ ክፍያው

ከላይ የተጠቀሱትን ዶክመንቶችና በChecklist የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ሳያሟላ የሚቀርብ ማንኛውም የፓስፖርት ማመልከቻ ለአመልካቹ ተመላሽ ይደረጋል፡፡

ለተጨማሪ ማብራሪያ  Passport Application Kit ይመልከቱ፡፡

የፎቶግራፍ ይዘት የሚከተሉትን ማሟላት ይኖርበታል

  • §   መጠኑ 3x4 cm የሆነ፣ የአመልካቹ ፊት መጠን በፎቶው ላይ ከጠቅላላ ፎቶግራፍ መጠን ከግማሽ የማያንስ፣

  • §   ጥላ የሌለበት፣ ከንፈር የተገጠመ፣ ሁለቱ ጆሮዎችን በሚገባ የሚያሳይ፣

  • §   ፊት ለፊት የተነሳ፣ ነጣ ያለና Smooth የሆነ የፎቶግራፍ ጀርባ /BACKGROUND/ ያለው፣

  • §   ያለመነጽር የተነሳ ቢሆን ይመረጣል፣

  • §   ከእምነት ጋር የተያያዘ እስካልሆነ ድረስ ኮፍያ ወይም የራስ መሸፈኛ የሌለበት፣

  • §  በፎቶግራፉ ጀርባ ላይ ስም ከነአያት የተመጻፈበት፣

  • ላይ የተጠቀሱትን የማያሟላ ማንኛውም ፎቶግራፍ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡

የክፍያ ዝርዝር ሁኒታ

  • ለማንኛውም ፓስፖርት አገልግሎ ክፍያ 500 የስዊድን ክሮነር ሲሆን ክፍያው በኤምባሲው Postgiro No. 629247-8 ወይም የባንክ አካውንት (Nordea Bank IBAN No. SE62 9500 0099 6026 0629 2478, SWIFT-Code NDEASESS)በቅድሚያ ከፈል ይኖርበታል፡፡ 

  • በአካል ቀርበው የሚያመለክቱ በካሽ መክፈል ያችላሉ፣

  • ማንኛውም ክፍያ በስዊድን ክሮነር መፈፀም ያኖርበታል፣

  • ከስዊድን ውጭ በባንክ ለሚፈፅሙት ማንኛውም ክፍያ ለባንክ ኮሚሽን *Bank Transfer Charge 60 የስዊድን ክሮነር ተጨምሮ 560 የስዊድን ክሮነር ከዋናው ክፍያ ጋር አብሮ ማስተላለፍ ይጠበቅባቸዋል፡፡

  • ለህፃናትና (ከ7 አመት በታች) ለመደበኛ ተማሪዎች (ከሚማሩበት የትምህርት ተም በመደበኛነት በመማር ላይ ያሉ መሆናቸውን የሚገልፅ ትክክለኛ ማስረጃ ከሚማሩበት ተቋም ካቀረቡ) 250 የስዊድን ክሮነር (በባንክ ከስዊድ ውጭ ለሚፈፀም ክፍያ 60 የስዊድን ክሮነር ይጨመራል )

  • ማንኛውም አመልካች ክፍያ የፈፀመበት ደረሰኝ ላይ ሙሉ ስሙን ፅፎ ከማመልካቻው ጋር አያይዞ መላክ አለበት፡፡ ክፍያው በሌላ ሰው የተፈፀመ ከሆነ ክፍያ የተፈፀመለት ሰው ስም በትክክል መፃፍ ይኖርበታል፡፡

  • ንም አይነት ክፍያ በፖስታ መላክ አይቻልም፡፡

  • ክፍያ መፈፀሚያ

    • በNordea Bank IBAN No. SE62 9500 0099 6026 0629 2478, SWIFT-Code NDEASESS ወይም

    • በPostgiro No. 629247-8 በቅድሚያ መፈፀም ይኖርበታል፡፡

የመላኪያ ፖስታ ይዘት

ለፖስታ መላኪያ ምንም አይነት ክፍያ ተቀባይነት የለውም፡፡ በመሆኑም

  • ከስዊድን ውስጥ በፖስታ ለሚቀርቡ የፓስፖርት ማመልከቻዎች ፖስፖርቱ ከተሰራ በኋላ መልሶ ለመላኪያ 68 የስዊድን ክሮነር ቴምብር የተለጠፈበት ኢንቨሎ መላክ የንርበታል፡፡

  • ከስዊድን ውጭ ካሉ ሀገሮች በፖስታ ለሚቀርቡ ማመልከቻዎች ፖስፖርቱ ከተሰራ በኋላ መልሶ ለመላኪያ የሚሆን የተቀባይ አድራሻ በግልፅ የተፃፈበት ባዶ ኢንቨሎከ9 ኢንተርናሽናል ኮፖን  ለ1 ፓስፖርት፣ 11 ኮፖን ለ2 ፓስፖርት፣ አብሮ መላክ ይኖርበታል፡፡ ከሁለት በላይ በአንድ ላይ ከስዊድን ለሚላኩ ፓስፖርቶች ለእያንዳንዱ ተጨማሪ ፓስፖርት ሶስት ተጨማሪ ኢንተርናሽናል ኮፖን መላክ ይኖርበታል፡፡

 

ማሳሰቢያ

  • ለፓስፖርት የሚቀርቡ ማመልቻዎች ወደዋና የኢሚግሬሽንና የዜግነት ጉዳይ መ/ቤት  እየተላኩ አዲሱን ማሽን ሪደብል ፓስፖርት በመሰጠት ላይ መሆኑ ይታወቃል፡፡ በመሆኑም ለአዲስ ፣ ለቅያሬ ፣ ለእድሳት ፣ በጠፋ ምትክ ለሚሰጥ ወይም ለማንኛውም አይነት የፓስፖርት አገልግሎት የሚቀርብ ማንኛውም የማመልካቻ ቅፅ በሁለት ኮፒ እንዲሁም  እያንዳንዱ ኦሪጅናል ሰነድ  ከሁለት ፎቶ ኮፒ ጋር ተያይዞ መቅረብ ያኖርበታል፡፡

  • ዚሁ መሰረት ቀደም ሲል በማንዋል ዘዴ የተሰጠ ማንኛውም ፓስፖርት (ባለ ሰማያዊ  ቀለም  ፓስፖርት) ንዲሁም ማሽን ሪደብል ፓስፖርት (ባለ ቡኒ ቀለም ፓስፖርት) ፀንቶ የሚያገለግልበት ጊዜ ሲያባቃ በሌላ አዲስ ፓስፖርት የሚቀየር ይሆናል፡፡

  • ግንቦት 01 ቀን 2011ዓ.ም ጀምሮ ቀደም ሲል የጣት አሻራ በመስጠት አዲሱን ማሽን ሪደብል (ባለ ቡኒ ቀለም) ፓስፖርት የወሰዱ አመልካቾች ፓስፖርቱ ፀንቶ የሚያገለግልበት ጊዜ ሲያበቃ በአዲስ ፓስፖርት ለመቀየር ለሚያቀርብ ማመልከቻ የጣት አሻራ መስጠት አያስፈልጋቸውም መሆኑን እንገልፃለን፡፡  

  • በመሆኑም ከሚያዚያ 01 ቀን 2002 ዓም ጀምሮ ፓስፖርት እድሳትም ሆነ ለቅያሬ የሚቃርብ ማመልከቻ ከ2 እስከ 3 ወር ጊዜ የሚወስድ መሆኑ ታውቆ ተገልጋዮች ማመልከቻዎቻቸውን ቀደም አርገው እንዲልኩ እናስገነዝባለን፡፡

  • ከኢትዮጵያ የሚወጡ (የሚሰጡ) ማንኛውም ሰነዶች ለምሳሌ የልደት የምስክር ወረቀት፤ የጋብቻ የምስክር ወረቀት፤ የትምህርት ማስረጃ፤ የመንጃ ፈቃድ … ወዘተ ከኤምባሲው ለሚጠየቁ አገልግሎቶች እንዲውሉ ከመቅረባቸው በፊት በኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተረጋገጡ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡

APPLICATION FORMS

 

1. For New Passport Applicants

2. In Replacement for Damaged or Expired Passport

 

3. In Replacement for Lost Passports 

 

4. For children passport

Samplesof registration papers/ የምዝገባ ሰነድ ናሙናዎች

NOTICE

 

The Ethiopian Embassy in Stockholm is currently processing to issue only a new electronic passport that requires mandatory fingerprints.

Starting from April 2010, to obtain a New, Replacement of lost, existing passport or renewal of a passport, fingerprints must be provided.

The Embassy also advice all applicants to submit their application at least 2 to 3 months ahead of their planned travel date or prior to applying for any other services that requires a valid passport.

 

After applying for a passport

 

  • After the passport division receives your application it will be reviewed to make sure it is complete.

  • If your application is incomplete, your original documents will be returned to you unprocessed. The Passport Division will send you a letter explaining why your application has been returned.

  • If your application is complete, you will receive a confirmation through email message.

  • If you move or change your address, email address, telephone number or any other contact information while your application is being processed, you must notify the passport division through email.

 

*** Your application will be returned if you do not provide all the requested information and documents listed under the CHECKLIST and fees.

 

Postal Address

Embassy of the Federal Democratic Republic of Ethiopia

P. O. Box 10148
100 55 STOCKHOLM, SWEDEN

 

E-mail

ethemb.community@telia.com

 

Telephone hours

13:00 PM - 15:30 PM HRS

Tel.004686616158 

(For Passport Issues)

 

Visiting hours for Consular Services

9:00 AM - 12:00 AM 

 

Fax Numbers

+ 46 86608177

+ 46 86609561

 

 

 

 

 

 

 


www.ethemb.se | ©2006 Embassy of FDRE All Rights Reserved | ethemb.all@telia.com| ethemb.community@telia.com