የግልና የቤት ውስጥ መገልገያ ዕቃዎችን በልዩ መብት ከታክስና ከቀረጥ ነፃ ወይም በታክስና ቀረጥ
ማስገባት ስለሚቻልበት ሁኔታ
የግልና የቤት ውስጥ
መገልገያ ዕቃዎች ዝርዝር
የኢትዮጵያ መንግስት
ልዑካን በተጨማሪ የሚያስገቡዋቸው ዕቃዎች ዝርዝር
የቀረጥና ታክስ ነፃ መብት ተጠቃሚ ለመሆን አመልካቾች ማሟላት የሚጠበቅባቸው መረጃዎች
1.
ኢትዮጵያውያን
(ቋሚ የመኖሪያ ፍቃድ ያላቸው ወይም ጊዜያዊ የመኖሪያ ፈቃድ ያላቸው ወይም በስደተኛ ካምፕ የሚኖሩ)፣
1.1.
ኦሪጅናል ፓስፖርት
§ ገፅ
1 (ለአዲሱ ፓስፖርት) ወይም ከገጽ
1-7 እና የቅርብ ጊዜ ዕድሣቱን የሚያሳየውን ገጽ ኮፒ
(ለድሮው ፓስፖርት)፣
§ ስደተኛ
ከሆኑ ከፖሊስ ወይም ከኢሚግሬሽን የተሰጠ የምዝገባ መረጃ፣
§ ተማሪ
ከሆኑ ከገጽ 1-7 እና የቅርብ ጊዜ ዕድሣቱን የሚያሳየውን ገጽ እና በፓስፖርቱ ላይ ተማሪነትዎን
የሚያሳይ የመኖሪያ ፍቃድ ያለበት ገጽ ኮፒ ሁሉም፣
1.2.
ከሚኖሩበት አገር ከታክስ ባለሥልጣን የቆይታ ጊዜን የሚያሳይ መረጃ፣
1.3.
ተማሪ ከሆኑ ትምህርትዎን ከተከታተሉበት (የትምህርት ዕድል እንደተሰጠዎት የሚያሳይ፣
ትምህርትዎን እንደሚያጠናቅቁ ወይም ማጠናቀቅዎትን የሚገልጽ ሆኖ የጀመሩበትና ያጠናቀቁበትን ጊዜ
የሚያሳይ) ማስረጃ፣
1.4.
ከኢትዮጵያ በግል የስራ ዕድል አግኝተው የስራ ጊዜዎን ጨርሰው/አቋርጠው የሚመለሱ ከሆነ
ከሰሩበት መ/ቤት የሰሩበትን ጊዜ የሚያሳይና ባሉበት አገር ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተረጋገጠ መረጃ፣
1.5.
ጠቅለው የሚመለሱ ከሆነ
§ ጡረተኛ - የጡረታና ከታክስ ባለሥልጣን የቆይታ ጊዜን የሚያሳይ መረጃ፣
§ ሌሎች - ቋሚ የመኖሪያ አድራሻ (Registration
of moving abroad)
መቀየራቸውን የሚያሳይና ከታክስ ባለሥልጣን የቆይታ ጊዜንና አዲሱን አድራሻ የሚያሳይ መረጃ፣
2.
የኢትዮጵያ ተወላጅ መታወቂያ ካርድ የያዙ
2.1.
ከፓስፖርት ውስጥ ፎቶግራፍ የሚገኝበት ገጽ ኮፒ፣
2.2.
የኢትዮጵያ ተወላጅ መታወቂያ ካርድ ኮፒ፣
2.3.
ጠቅለው የሚመለሱ ከሆነ
§
ጡረተኛ - የጡረታና ከታክስ ባለሥልጣን የቆይታ ጊዜን የሚያሳይ መረጃ፣
§ ሌሎች - ቋሚ የመኖሪያ አድራሻ (Registration
of moving abroad)
መቀየራቸውን የሚያሳይና ከታክስ ባለሥልጣን የቆይታ ጊዜንና አዲሱን አድራሻ የሚያሳይ መረጃ፣
ማሳሰቢያ:-
v
በስዊድን ነዋሪ የሆኑ የሚላክላቸውን የቀረጥና ታክስ ነፃ መብት ተጠቃሚ ለመሆን የሚያስችላቸውን ደብዳቤ
መላኪያ፣ የመመለሻ አድራሻ የተዘጋጀበት ባለ 5ዐ ክሮነር ስታምፕ የተለጠፈበት የተዘጋጀ ፖስታ አብሮ
መላክ፣
v
ከስዊድን ውጭ የሚኖሩ የሚላክላቸው የቀረጥና ተክስ ነፃ መብት ተጠቃሚ ለመሆን የሚያስችላቸውን ደብዳቤ
መላኪያ፣ የመመለሻ አድራሻ የተዘጋጀበት ፖስታና የ1ዐዐ ክሮነር የተመጣጣኝ የሆነ ዋጋ ያለው
ኢንተርናሽናል ኩፖን መላክ ይኖርባቸዋል፡፡
The Application Form
For further information you may
refer to:
Cutstom Authority's
Home Page