HomeEthiopiaEthiopian NewsThe EmbassyConsular/VisaCommunityTradeInvestmentTourismLinks

Consular/VisasPassport IssuesEthiopian Origin IDCertificate of IdentityLaissez-PasserLegalizationDuty Free Benefits

 

 

የትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርድ/

Ethiopian Origin ID


ትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርድ መሟላት ያለባቸው

01. ለአዲስ የትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርድ

  1. በሁለት ኮፒ በሚገባ ተሞልቶ የተፈረመ የአዲስ ትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርድ ማመልከቻ ቅፅ /001 ወይም 002 ቅጹን በሁለት ኮፒ ይሙሉ/፣

  2. በቅርብ ጊዜ የተነሳና ሙሉ ፊትን የሚያሣይ 3x4 የሆኑ 3 ፎቶግራፎች ከማመልከቻ ቅጽ ጋር ያያይዙ፣

  3. ከቅጹ ጋር ኢትዮጵያዊ ተወላጅ መሆንዎን የሚያረጋግጥ ሰነድ ዋናውንና ከየዓይነቱ ሁለት ኮፒ ያያይዙ፣

  4. ዜግነት ከወሰዱበት ሀገር አግባብ ካለው አካል የፀና ኦሪጅናል ፓስፖርት እና በአገሩ የተመዘገቡበትን ሰነድ /Personbevis-Sweden, Folkeregister-Denmark, Folkeregister-Norway, Extrat from the Population Information System-Finland, Einstaklingar-Iceland/ ያቅርቡ፣/ ሪጅናል ፓስፖርትዎን ይላኩ/

  5. መታወቂያውን ለመውሰድ በአካል ቀርበው ለሚያመለክቱ 5ዐዐ.ዐዐ የአሜሪካን ዶላር ወይም ክፍያውን በኤምባሲው PlusGirot ባንክ የሚፈፅሙ ከሆነ 5ዐዐዐ.ዐዐ የስዊድን ክሮነር የሚያስፈልግ ሲሆን ክፍያው በ IBAN No.  SE62 9500 0099 6026 0629 2478, SWIFT-Code NDEASESS, ወይም PlusGirot  No. 629247-8. መፈፀም ይኖርበታል፡፡ እንዲሁም ለባንክ ኮሚሽን 60 ክሮነር እና የፖስታ መልሶ መላኪያ 100 ክሮነር ተጨማሪ ክፍያ ማስተላለፍ ይጠበቅባቸዋል፡፡

      ክፍያን በፖስታ መላክ አይቻልም፡፡

  6. የሚጠይቁት መታወቂያ በጋብቻ ከሆነ እንደአግባብነቱ ጋብቻው ሁለት ዓመት የፀና መሆኑን የሚያሳይ ማረጋገጫ ሰነድና የአመልካቹ/ቿ ባል/ሚስት ያወጣውን/ያወጣችውን የኢትዮጵያ ተወላጅ መታወቂያ ካርድ ወይም በአገልግሎት ላይ ያለ የኢትዮጵያ ፓስፖርት  በማያያዝ ያቅርቡ፣

  • አስራ ስምንት ዓመት ያልሞላቸው ልጆችዎን የልደት የምስክር ወረቀት ወይም ተመሳሳይ መረጃ በማቅረብ በወላጅ መታወቂያ ላይ በማስመዝገብና በልጆቹ ፓስፖርት ላይ የኢትዮጵያ ተወላጅ ማህተም በማስደረግ የተለያዩ አገልግሎቶችን እንዲያገኙ ያስችላቸዋል::

    / አስራ ስምንት ዓመት ያልሞላቸው ልጆችዎን  ኦሪጅናል ፓስፖርት ይላኩ/

የኢትዮጵያ ተወላጅ መታወቂያ ካርድ የመጠየቂያ ቅጽ አሞላል ማብራሪያ

  • . ቅጾቹ በሙሉ የሚሞሉት በራሱ በአመልካቹ ብቻ ይሆናል፡፡

  • .  ቅጾቹን በጥንቃቄና በግልጽ ይሙሉ፣

  • .  በቅጾቹ ላይ የአመልካች ሙሉ ስም በአማርኛና በእንግሊዝኛ ቋንቋዎች ይሞሉ፣

  • .  ከስም በስተቀር የቅጹን ቀሪ ክፍል አመልካች በመረጡት በእንግሊዝኛ ወይም በአማርኛ ቋንቋ መሙላት ይችላሉ፣

  • .  በቅጹ ላይ መሞላት ያለበት ቀን፣ ወር፣ ዓመተ ምህረት (ዘመን) አመልካች በኢትዮጵያ ወይንም እ.ኤ.አ. መርጠው መሙላት ይችላሉ፡፡ ሆኖም በሰነድ ላይ የሚታይ ከሆነ በሰነዱ ላይ በተጻፈበት የዘመን አቆጣጠር ይጠቀሙ፣


02. ትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርድ እድሳት

  • የሚታደሰውንትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርድ፣ 

  • በሁለት ኮፒ በሚገባ ተሞልቶ የተፈረመ ትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርድ የእድሳት ማመልከቻ ቅፅ /003  በሁለት ኮፒ ይሙሉ/፣

  • በቅርብ ጊዜ የተነሳና ሙሉ ፊትን የሚያሣይ 3x4 የሆኑ 2 ፎቶግራፎች ከማመልከቻ ቅጽ ጋር ያያይዙ፣

  • ዜግነት ከወሰዱበት ሀገር አግባብ ካለው አካል የተሰጠና የፀና ኦሪጅናል ፓስፖርት እና በአገሩየተመዘገቡበትን ሰነድ /Personbevis-Sweden, Folkeregister-Denmark, Folkeregister-Norway, Extrat from the Population Information System-Finland, Einstaklingar-Iceland/ ያቅርቡ፣/ ሪጅናል ፓስፖርትዎን ይላኩ/

 

ክፍያ

  • 200 የአሜሪካ ዶላር ወይም 2000 የስዊድን ክሮነር ካርድ እድሳት

  • 200 ዶላር ወይም 2000 የስዊድን ክሮነርበጥፋ ምትክ ለሚሰጥ

ማስታወሻ፡-

 በስዊድን ነዋሪ የሆኑ የተዘጋጀላቸውን የትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርድ የመመለሻ አድራሻ በግልፅ የተፃፈበትና ባለ 61 ክሮነር ስታምፕ/ቴምብር የተለጠፈበት ፖስታ አብሮ መላክ፣

 ከስዊድን ውጭ የሚኖሩ የተዘጋጀላቸውን የትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርድ መመለሻ አድራሻ በግልፅ የተፃፈበት ፖስታና  የ1ዐዐ ክሮነር የተመጣጣኝ የሆነ ዋጋ ያለው ኢንተርናሽናል ኩፖን መላክ ይኖርባቸዋል፡፡

ኤምባሲው ለአገልግሎቱ ከሚጠይቀው የክፍያ መጠን እንዲሁም የባንክ ኮሚሽንና የፖስታ መላኪያ ገንዘብ ውጭ የሚፈፀም ማንኛውም በትርፍ ገቢ የሆነ ገንዘብ የማይመለስ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

Payment can be made through

 

Nordea Bank

IBAN No. SE62 9500 0099 6026 0629 2478, SWIFT-Code NDEASESS, 

OR  Postgiro No. 629247-8.

 

 

የኢትዮጵያ ተወላጅነት መታወቂያ ካርድ የያዙ የውጭ ዜጎች መብቶችና ገደቦች

 

1. መብቶች

በአዋ ጥር 270/2002 በተደነገገው መሠረት የፀና የኢትዮጵያ ተወላጅነት መታወቂያ ካርድ ያለው ማንኛውም የውጭ አገር ዜጋ በዚህ አንቀጽ ስር የተዘረዘሩት መብቶች ተጠቃሚ ይሆናል፡፡

  1. ወደ ኢትዮጵያ ለመግባትና ኢትዮጵያ ውስጥ ለመቆየትም ሆነ ለመኖር የመግቢያ ቪዛና የመኖሪያ ፈቃድ እንዲኖረው አይጠየቅም፡፡

  2. ከሀገር መከላከያ፣ ከሀገር ደህንነት ወይም ከውጭ ጉዳይና መሰል የፖለቲካ የመንግስት መ/ቤቶች በስተቀር የሥራ ፈቃድ እንዲያወጣ ሳይገደድ በኢትዮጵያ ውስጥ ተቀጥሮ መስራት ይችላል፡፡

  3. አግባብ ባለው የጡረታ ሕግ የውጭ ዜጎች የመብት ተጠቃሚ እንዳይሆኑ የሚገድበው ድንጋጌ ተፈጻሚ አይሆንበትም፡፡

  4. የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለቤትነት መብት ይኖረዋል፡፡

  5. እንደ ሀገር ውስጥ ባለሀብት መቆጠር ከፈለገ በሀገሪቱ የኢንቨስትመንት ሕግ መሠረት ለሀገር ውስጥ ባለሀብት በተፈቀዱ የኢንቨስትመንት መስኮች መሳተፍ ይችላል፣

  6. የኢኮኖሚ፣ የማኀበራዊና አስተዳደራዊ አገልግሎቶችን በመጠቀም ረገድ በውጭ ዜጎች ላይ በሕግ፣ በመመሪያ ወይም በአሰራር ልምድ የተጣሉ ገደቦችና የሚደረጉ ልዩነቶች አይመለከቱትም፡፡

2. ገደቦች

  1. ከላይ የተጠቀሱት መብቶች ቢኖሩትም የኢትዮጵያ ተወላጅነት መታወቂያ ካርድ የያዘ የውጭ ዜግነት ያለው ሰው ነው፣
  2. በማናቸውም የመንግስት ደረጃ በሚካሄድ ምርጫ የመምረጥና የመመረጥ መብት አይኖረውም፣
 

 

 Requirements to Receive Identification Card of Ethiopian Origin

1.  General Information

·  Interested foreign nationals of Ethiopian origin are entitled to receive the ID card as per proclamation No 270/2002.

·  Children under 18 can enjoy the same right once their name appear in their parents ID card of Ethiopian origin. A spouse of foreign national of Ethiopian origin, if wish so, can also receive the ID card

·  The holder of the ID card can enjoy every right like other citizens with the exception of political right. (For more information refer the proclamation Ethiopian Origin ID Card.) PDF

2. Privileges given to  the Holder of the ID Card of Foreign Nationals of Ethiopian Origin

The holder shall:

·  Not be required to have an entry visa or residence permit to live in Ethiopia;

· Have the right to be employed in Ethiopia without a work permit;

· Not be subjected to the exclusion that applies to foreign nationals regarding coverage of pension scheme under the relevant pension law,

·  have the right to be considered as domestic investor to invest in Ethiopia under Investment law of Ethiopia.

·  Restrictions imposed on foreigners regarding the utilization of Economic, Social and Administrative Services shall not be applicable to the holder of the ID card.

3Application Procedure:

· Applicant should fill two copies of Formo1 with three photos (3x4 sizes) and submit it together with supportive documents that prove his claim.

These documents include the following:

· Copy of Ethiopian passport the applicant had previously or birth certificate,

· Copy of parent’s ID card,

· Letter of testimony from office of  Kebele council where applicant’s parents reside or used to reside in Ethiopia; and,

· Any document including educational credential, bank book or others that help to establish the applicant’s origin.

· Form 002 should be filled if the applicant is spouse of foreign national of Ethiopian origin .The first part of the statement in Form 002 should be filled out and signed by the holder of the ID card whose spouse is applying to get ID card.

· The supporting documents have to be authenticated relevant offices or our Embassy. Any document that would be brought from Ethiopia as supporting document like a document given by local administration (kebele) should be certified by the Ministry of Foreign Affairs of Ethiopia.

When the documents are accepted, the applicant would be notified of the Embassy’s decision.

4. Payment

  • The payment for the ID should 500USD dollar if the applicant come in person at the embassy and pay in cash. To send back the passport and ID Card by registered mail to your address, applicant from Sweden has to enclose a pre-addressed envelop with 65 Swedish Kronor stamps and applicant from outside Sweden has to enclose a pre-addressed envelop with 9 International coupons for the weight up to 100 grams.

  • If the payment made through bank, the applicant should have to transfer 5000SEK to Embassy‘s account in Stockholm.

  • In addition to the ID fee, the applicant  from Sweden should pay 65SEK for Swedish Postal transfer charge. But applicant outside Sweden should pay 60SEK for Swedish Bank Commission and 100SEK Postal transfer charge OR enclose a pre-addressed envelop with 9 International coupons for the weight up to 100 grams or 11 International coupons for the weight up to 250 grams or 14 International coupons for the weight up to 500 grams, to enable us to send back your passport and ID Card by registered mail to your address instead of paying 100SEK Postal transfer charge.

Notes:-

· The required Bank commission should be borne by the applicant. The applicant then should send bank deposit receipt together with his/her valid passport and other application documents to the Embassy.                    

. The newly issued Identity Card together with the applicant’s passport (on which a stamp will be affixed) will then be sent back to the applicant.

Application Forms ማመልከቻ ቅጾች

 

01. ለአዲስ የትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርድ ማመልከቻ ቅፅ

01. For New Ethiopian Origin ID Application Form

02. ትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርድ እድሳት ቅፅ

Ethiopian Origin ID Renewal Form

003. (PDF)

Postal Address

Embassy of the Federal Democratic Republic of Ethiopia

P. O. Box 10148
100 55 STOCKHOLM, SWEDEN

Telephone

Tel. +46 8 665 60 30 (Consular section Ext.1,2,6 or 9,)13:30 PM -15:30PM HRS

Fax +46 86609561

 


www.ethemb.se | ©2006 Embassy of FDRE All Rights Reserved | ethemb.community@telia.com | ethemn.all@telia.com

Design by AG