VISA AND OTHER CONSULAR MATTERS

Visa  |  Passport   Ethiopian Origin ID  Certificate of National Identity   |  Laissez Passer Legalisation   Duty and Duty Free

የይለፍ ሰነድ (ሊሴፓሴ) አሰጣጥ ሁኔታ - Laissez-Passer Application

1.1     በግንባር ቀርበው ለሚያመለክቱ

§   አመልካች በአካል ቀርቦ ለዚህ አገልግሎት ተብሎ በተዘጋጀው ቅጽ ላይ መረጃዎችን በተሟላ መልኩ ተሞልቶ ሲቀርቡ (በሁለት ኮፒ)፣

§   ኢትዮጵያዊነትን ሊያረጋግጡ የሚችሉ መረጃዎች /መታወቂያ፣ መንጃ ፈቃድ፣ የትውልድ ሰርተፍኬት፣ ወዘተ/ ሲቀርብ፣

§   የግራና የቀኝ እጅ አመልካች ጣቶች አሻራ ሲሰጥ፣

§   አራት ፎቶግራፍ መጠኑ 3x4 cm የሆነ መስጠት፣

§  ከሚኖሩበት ኢሚግሬሽን ወይም ከፖሊስ የተሰጠ የምዝገባ ሰነድ (ዜግነትን በሚያሳይ መልኩ) ማረጋገጫ ወረቀት  

§   ክፍያ ሲፈጸም፣

1.2     የኢትዮጵያ ሚሲዮኖች በሌሉባቸው አገሮች በግንባር ቀርበው ማመልከት ለማይችሉ

§   የሊሴፓሴ መጠየቂያ ቅጽ በሁለት ቅጂ ተሞልቶ ሲቀርብ፣

§   ሊሴፓሴ እንዲሰጠው በጽሑፍ ማመልከቻ ሲያቀርብ፣

§   ኢትዮጵያዊነቱን ሊያረጋግጡ የሚችሉ ማስረጃዎች /መታወቂያ፣ መንጃ ፈቃድ፣ ወዘተ/ ሲያቀርብ፣

§   ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የአሻራ መስጫ ፎርም ላይ የግራና የቀኝ እጅ አመልካች ጣቶች አሻራ በፎርሙ ላይ በአካባቢው ፖሊስ ፊት ቀርቦ ሲነሳና አሻራው የግለሰቡ መሆኑ በፖሊስ ጣቢያው የጽሑፍ መግለጫ ሲሰጠው ወይም በፐብሊክ ኖታሪ ወይም ተመሳሳይ ሕጋዊነት ባለው አካል ሲረጋገጥና ይኸውም በሚኖሩበት ሀገር በየሀገራቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተረጋገጠ መሆን ይኖርበታል

§   አራት ፎቶግራፍ መጠኑ 3x4 cm የሆነ ሲያቀርብ፣

§   በደንቡ መሠረት የሊሴፓሴ  ክፍያውና የፖስታ መላክያውም ጭምር ሲልክ፣

ክፍያ

  • 200 የስዊድን ክሮነር

  • ከስዊድን ውጭ በባንክ ለሚፈፀም ክፍያ 60 ስዊድን ክሮነር ለባንክ ማስተላለፊያ (BANK TRANSFER CHARGE) ጭማሪ ክፍያ መከፈል ይኖርበታል

  ► ክፍያ የተፈፀመበት ደረሰኝ ከማመልከቻው ጋር ተያይዞ መላክ ይኖርበታል፡፡

 ► ክፍያን በፖስታ መላክ አይቻልም፡፡

 

ክፍያ የሚፈፀምበት

  • Nordea Bank

    IBAN No. SE62 9500 0099 6026 0629 2478, SWIFT-Code NDEASESS, 

  • OR  Postgiro No. 629247-8.

ማሳሰቢያ

 

በስዊድን ነዋሪ የሆኑ የተዘጋጀላቸውን የይለፍ ሰነድ /ሌሴ ፓሴ የመመለሻ አድራሻ የተዘጋጀበት ባለ 68 ክሮነር ስታምፕ የተለጠፈበት የተዘጋጀ ፖስታ አብሮ መላክ፣

   ከስዊድን ውጭ የሚኖሩ የተዘጋጀላቸውን የይለፍ ሰነድ /ሌሴ ፓሴ የመመለሻ አድራሻ የተዘጋጀበት ፖስታና የ1ዐዐ ክሮነር የተመጣጣኝ የሆነ ዋጋ ያለው ኢንተርናሽናል ኩፖን መላክ ይኖርባቸዋል፡፡

    ► ኤምባሲው ለአገልግሎቱ ከሚጠይቀው የክፍያ መጠን እንዲሁም የባንክ ኮሚሽንና የፖስታ መላኪያ ገንዘብ ውጭ የሚፈፀም ማንኛውም በትርፍ ገቢ የሆነ ገንዘብ የማይመለስ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

 

 

 

የይለፍ ሰነድ (ሊሴፓሴ)

Laissez-Passer Application Form

PDF FILE

 

ጣቶች አሻራ መስጫ ቅፅ

Finger Print Form 

(PDF FILE)

 

Postal Address

Embassy of the Federal Democratic Republic of Ethiopia

P. O. Box 10148
100 55 STOCKHOLM, SWEDEN

 

 

E-mail

ethemb.community@telia.com

 

Telephone hours

13:00 PM - 15:30 PM HRS

Tel.004686616158 

(For Laissez-Passer issues)

 

Visiting hours

9:00 AM - 12:00 AM (Visiting hours) 

 

 

 

 

 


www.ethemb.se | ©2006 Embassy of FDRE All Rights Reserved | ethemb.community@telia.com